በኦሮሚያ ክልል በፀጥታ ችግር ምክንያት የተጎዱ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶችን የመጠገን ስራ ተጀምሯል ተባለ
TRACK

በኦሮሚያ ክልል በፀጥታ ችግር ምክንያት የተጎዱ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶችን የመጠገን ስራ ተጀምሯል ተባለ

00:00

ግንቦት 29፣2016

በኦሮሚያ ክልል በፀጥታ ችግር ምክንያት የተጎዱ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶችን የመጠገን ስራ ተጀምሯል ተባለ፡፡

በጦርነት ምክንያት ስርቆት ወይም ብልሽት ደርሶባቸው ጥገና እየተደረገላቸው ነው የተባሉት የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች ምን ያህል የዋጋ ግምት እንደሚያወጡ አልተነገረም፡፡

በክልሉ የተለያዩ አካባዎች በሚያጋጥሙ የፀጥታ ችግሮች የተነሳ በአራቱም የወለጋ ዞኖች የተጎዱ የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማቶችን ጠግኖ ወደ ስራ ለማስገባት ስራ ጀምሬአለው ያለው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ነው፡፡

የጥገና ስራው የሚከናወነው በምዕራብ ወለጋ፣ ምስራቅ ወለጋ፣ ሆሩጉድሩ እና ቄለም ወለጋ ዞኖች በነበረው የፀጥታ ችግር ምክንያት በደረሰ ኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት ውድመት ምክንያት ሃይል ተቋርጦባቸው በነበሩ አንድንድ አካባቢዎች ነው ያሉት የአገልግሎቱ የኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ መላኩ ታዬ በክልሉ አንፃራዊ ሰላም ባሉባቸው አካባቢዎች የጥገና ስራው እየተከወነ ነው ብለዋል፡፡

በክልሉ የተለያዩ አካባዎች በሚያጋጥሙ የፀጥታ ችግሮች ምክንያት ምን ያህሉ የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማቶቹ ጉዳት ደረሰባቸው፣ ምን ያህል በጀትስ ያስፈልገዋል፣ የጉዳቱ መጠን እስከምን ድረስ ነው፤ የሚለውን ጨምሮ ሌላውንም ለመለየት እና ጥናት ለማድረግ ጊዜ የለንም የቅድሚያ ቅዲሚያ መሰጠት ያለበት ህብረተሰቡ የኤሌክተሪክ አገልግሎት እንዲያገኝ ማድረግ ነው ያሉት አቶ መላኩ ከጥገናው በኋላ የጉዳቱ መጠን እና የወጣው ወጭን አገልግሎቱ ያሳውቃል ብለዋል፡፡

ፋሲካ ሙሉወርቅ

Comments

00:00