የአዕምሮ ህክምና አገልግሎቱ ካለፉት ዓመታት እየተሻሻለ ቢመጣም አሁንም ግን እርዳታ የሚፈልጉ ዜጎችን ያህል በስፋት አልተሰራበትም ተባለ
TRACK

የአዕምሮ ህክምና አገልግሎቱ ካለፉት ዓመታት እየተሻሻለ ቢመጣም አሁንም ግን እርዳታ የሚፈልጉ ዜጎችን ያህል በስፋት አልተሰራበትም ተባለ

Avatar

ሰኔ 21፣ 2016

የአዕምሮ ህክምና አገልግሎቱ ካለፉት ዓመታት እየተሻሻለ ቢመጣም አሁንም ግን እርዳታ የሚፈልጉ ዜጎችን ያህል በስፋት አልተሰራበትም ተባለ፡፡

መሰረታዊ የሆኑ የስነ-ልቦና የምክር አገልግሎትን ጨምሮ የመጀመሪያ ደረጃ የአዕምሮ ህክምና አገልግሎቶች በየጤና ተቋማት መሰጠት መጀመሩ የታየ ለውጥ ነው ተብሏል፡፡

ካለፉት ዓመታት አኳያ የአዕምሮ ጤና ህክምናው ላይም ይሁን የባለሞያዎቹ ቁጥር ከፍተኛ መሻሻል መኖሩን የነገሩን የአዕምሮ ህክምና ስፔሻሊስቱ ፕሮፌሰር አታላይ አለም ናቸው፡፡

ነገር ግን በሀገሪቱ ካለው የአዕምሮ ህክምና አገልግሎት ፈላጊ ጋር ሲተያይ አሁንም ቁጥሮቹ ትንሽ ናቸው ብለዋል፡፡

በተለይ ከመድኃኒት አቅርቦት ጋር እንዲሁም ቅድሚያ እንደተላላፊ ላሉ ህመሞች ከመሰጠቱ አኳያ የአዕምሮ ህክምናው የተገባውን ያህል ትኩረት አልተሰጠውም ተብሏል፡፡

Comments

Avatar