ህዳር 9፣2017
የፓርኪንሰን ህሙማን የሚወስዱት መድኃኒት ከገበያ ከጠፋ ከ6 ወር በላይ እንደሆነ ታማሚዎችና አስተማሚዎች ተናገሩ፡፡
በህመሙ ላይ የመድኃኒቱ አለመኖር ተጨምሮበት ህመማችን እንዲባባስ አድርጎታል ሲሉ ህሙማኑ እና አስታማሚዎች ያስረዳሉ፡፡
ከዚህ ቀደም ይህ መድሃኒት፤ #ከነማ መድሃኒት ቤቶች የሚገኝ ሲሆን አሁን ላይ በየትኞቹም መድሃኒት ቤቶች እንደማይገኝ ከታማሚዎች ሰምተናል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ከነማ መድሃኒት ቤቶች እኔም መድሃኒቱን አግኝቼ ለህሙማኑ ለማቅረብ አልቻልኩም በዋናነት የሚመለከተው የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ ድርጅት ነው ብሏል፡፡
የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ በበኩሉ እጥረቱ መኖሩ አምኖ በግዢ ሂደት ላይ ነው ብሏል፡፡
Comments