ሰኔ 9 2017
የውጭ ዜጎች በኢትዮጵያ የማይንቀሳቀስ ንብረት ወይንም ይዞታ ባለቤት እንዲሆኑ የሚፈቅደው ረቂቅ ህግ ህገ መንግስቱን ይቃረናል የሚል ቅሬታ ከፓርላማው የህግ ክፍል ቀረበበት፡፡
የፍትህ ሚኒስቴር በበኩሉ መሬትን በይዞታነት ወይንም ደግሞ ቤትን ባለቤትነት መያዝ የሚከለክለው ህገ መንግስቱ ሳይሆን ፍትሐ ብሔር ነው ብሏል፡፡
በተጨማሪም ረቂቅ አዋጁ የካፒታል ሽሽትን ለያስከትል ይችላል ከኢትዮጵያውያን ባህል፣ ወግ ፣ እሴትና ሃይማኖት ጋር የሚቃረኑ ባህሎች ወደ አገሪቱ እንዲገቡ በር ከፋች ሊሆን ይችላል የሚል ትችትም ከምክር ቤት አባላት ቀርቦበታል፡፡
በረቂቅ አዋጁ ላይ ይህ ቅሬታ የቀረበበት የከተማ፣ መሰረተ-ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እና የሕግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በረቂቅ አዋጁ ላይ ይፋዊ ህዝባዊ ውይይት ባካሄደበት ወቅት ነው፡፡
Comments