ታህሳስ 25፣2017  - በአፋር ክልል ገቢረሱ ዞን የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ መከሰቱን ዞኑ ለሸገር ተናገረ
TRACK

ታህሳስ 25፣2017 - በአፋር ክልል ገቢረሱ ዞን የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ መከሰቱን ዞኑ ለሸገር ተናገረ

Avatar

ታህሳስ 25፣2017

በአፋር ክልል ገቢረሱ ዞን የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ መከሰቱን ዞኑ ለሸገር ተናገረ፡፡

ዛሬ ማለዳ 3 ሰዓት አካባቢ በዞኑ ዱለሳ ወረዳ ሰጋንቶ ቀበሌ ላይ ነው እሳተ ገሞራው የፈነዳው ተብሏል፡፡

በተጠቀሰው አካባቢ ያሉ ተራራ ላይ አዳዲስ ፍንዳታዎች መኖራቸውን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብዶ አሊ ነግረውናል፡፡

በፍንዳታው ከሚወጣ ጭስ ጋር አብሮ ጭቃ እየተትጎለጎለ ወደ ላይ ይፈናጠራል ያሉት አቶ አብዶ ጭቃው ሰውነት ላይ ካረፈ በጣም ያቃጥላል ይላሉ፡፡

ከሌሊቱ 9 ሰዓት ጀምሮ ዶፈን ተራራ ላይ የተለያዩ የእሳተ ጎመራ ፍንዳታዎች እንደተከሰቱ የተናገሩት የዞኑ አስተዳደሪ እሳቸው የሰሙት ግን ከማለዳው 3 ሰዓት ላይ የተከሰውን እንደሆነ ነግረውናል፡፡

Comments

Avatar