ግንቦት 13 2017
በአዲስ አበባ በመንገድ ላይ በሚደርሱ የትራፊክ አደጋዎች የሚከሰት የእግረኞች የአካል ጉዳት ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቷል ተባለ፡፡
በከተማዋ ከሚደርሱ የትራፊክ አደጋዎች ከአምስቱ አራቱ በመንገድ ተጠቃሚ እግረኞች ላይ የሚደርስ እንደሆነ ተነግሯል፡፡
ይህንን ያለው አመታዊው የመንገድ ደህንነትን የሚያሳየውና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣንና ብሉምበርግ በጎ አድራጎት ኢኒሼቲቭ ፎር ግሎባል ሮድሴፍቲ ጋር በመተባበር የተሰናዳ አመታዊ የመንገድ ደህንነት ሪፖርት ነው፡፡
የአዲስ አበባ አመታዊ የመንገድ ደህንነት ሪፖርቱ በመንገድ ተጠቃሚዎች ላይ የሚደርስ ሞት ከአጠቃላይ የትራፊክ አደጋ ከሚመዘገቡ ሞቶች 86 በመቶውን ይሸፍናሉ ብሏል፡፡
78 በመቶ የሚሆነው የትራፊክ አደጋ ሞት የሚከሰተውም በወንዶች ላይ ነው ተብሏል፡፡
Comments