‘’በአዲስ የተዋቀረው ካቢኔ በክልሉ ባለፉት 2 ዓመታት ታይቶ የነበረውን የዴሞከራሲ ልምምድ ወደ ቀድሞው የሚመልስ ነው’’ ተፎካካሪ ፓርቲዎች
TRACK

‘’በአዲስ የተዋቀረው ካቢኔ በክልሉ ባለፉት 2 ዓመታት ታይቶ የነበረውን የዴሞከራሲ ልምምድ ወደ ቀድሞው የሚመልስ ነው’’ ተፎካካሪ ፓርቲዎች

Avatar

ሚያዝያ 15 2017

በአዲስ የተዋቀረው ትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ በክልል ባለፉት ሁለት ዓመታት ታይቶ የነበረውን የዴሞከራሲ ልምምድ ወደ ቀድሞው ቦታው የሚመልስ ነው ሲሉ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ሶስት ተፎካካሪ ፓርቲዎች ተናገሩ፡፡

የአዲሱ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ አካታች ያልሆነ፤ ለክልሉም ሰላም የማያመጣ ነው ሲሉም ተፎካካሪ ፓርቲዎች ተችተዋል፡፡

በአዲሱ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዘዳንት በሌተና ጀነራል ታደሰ ወረደ ባለፈው የተዋቀረው ካቢኔ አካታች ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲኖር የሚያዘውን የሰላም ስምምነት የሚጥስ ነው ሲሉ ፓርቲዎቹ ተናግረዋል፡፡

በአዲሱ ካቢኔ ላይ ትችት ያቀረቡት ሳልሳይ ወያነ ትግራይ፣ ባይቶና እና አረና ፓርቲዎች ናቸው፡፡

ፓርቲዎቹ በአዲሱ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዘዳንት በጀነራል ታደሰ ወረደ የተዋቀረው ካቢኔ፤ ደብረፅዮን ገ/ሚካዔል(ዶ/ር) የሚመራው የህወሓት ቡድንን ወደ ቦታው እንዲመለስ ያደረገ ነው ሲሉ ተችተዋል፡፡

Comments

Avatar