የስኳር ህመም ከሚያስከትላቸው ቋሚ የጤና ችግሮች በተጨማሪ በህሙማኑ ላይ የሚያደርሰው የሥነ ልቦና ጫና ከፍተኛ እንደሆነ ባለሞያዎች ይናገራሉ፡፡
TRACK

የስኳር ህመም ከሚያስከትላቸው ቋሚ የጤና ችግሮች በተጨማሪ በህሙማኑ ላይ የሚያደርሰው የሥነ ልቦና ጫና ከፍተኛ እንደሆነ ባለሞያዎች ይናገራሉ፡፡

Avatar

ጥር 14 2017

የስኳር ህመም ከሚያስከትላቸው ቋሚ የጤና ችግሮች በተጨማሪ በህሙማኑ ላይ የሚያደርሰው የሥነ ልቦና ጫና ከፍተኛ እንደሆነ ባለሞያዎች ይናገራሉ፡፡

የአኗኗር ዘይቤን ማስተካከልና የአመጋገብ ሥርዓትን ማሻሻል የስኳር ህሙማን ሊጠነቀቁባቸው ከሚገቡ ጉዳዮች በብዛት የሚነገሩ ቢሆኑም የሥነ-ልቦናና የአህምሮ ጤናቸውም ጉዳይ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ተነግሯል፡፡

የስኳር ህመም ከሚያስከትለው ችግር አንዱ የሥነልቦና ጫናና የአህምሮ ጤና መታወክ መሆኑን የሚናገሩት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሥነ አህምሮ ሐኪም የሆኑት ዶክተር ናርዶስ ሰይፉ ናቸው፡፡

የሰውነት የስኳር መጠን ከፍ ወይም ዝቅ ማለት በአህምሮ ጤና ላይ በዛው ልክ ጫና ሊያሳድር እንደሚችል እና የአህምሮ ጤና ችግር ካለ የስኳር ህመም ተጋላጭነትን የሚጨምረውም በተለምዶ ጭንቀት ማብዛት የደም ውስጥ የስኳር መጠንን ከፍ ስለሚያደርግ የሥነ ልቦና ጫናና ስኳር ከፍተኛ ግንኙነት እንዳላቸው በዘርፉ የተከወኑ ጥናቶች ያሳያሉ ብለዋል፡፡

በብዛት ከሚታዩ የአእምሮ ህመም ችግሮች ውስጥ ድባቴ አንዱ መሆኑን የሚጠቅሱት ዶክተር ናርዶስ ይህ በስኳር ህሙማን ላይ ሲሆን ደግሞ በእጥፍ የሚታይ ነው ይላሉ፡፡

Comments

Avatar