00:00
ሚያዝያ 22 2017
በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የሚሰሩ ሴት ሰራተኞች የሚከፈላቸው ደመወዝ ኑሮን ለማሸነፍ ስላላስቻላቸው ማታ ማታ በወሲብ ንግድ የተሰማሩ መኖራቸውን በጥናት መለየቱን የጨርቃ ጨርቅ ፌዴሬሽን ተናግሯል፡፡
በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የሚሰሩ ሴት ሰራተኞች የሚከፈላቸው ደመወዝ ለኑሮ ስለማይበቃቸው ማታ ማታ ከሆቴሎች ትርፍራፊ ምግቦችን ይዘው ወደ ቤታቸው የሚገቡ እንዳሉም ፌደሬሽኑ ጠቁሟል፡፡
አምራች ስራተኛ፣ ምቹ ስራ ለወጣቶች እና ሴቶች በጨርቃ ጨርቅ አምራች ኢንዱስትሪዎች ውስጥ መፍጠር በሚል ርዕስ የፖሊሲ አቅጣጫ ተቋሚ ጥናት ለማድረግ የማህበራት ጥናት መድረክ (Forum For Social Studies) በጠራው የሁለተኛ ዙር የባለድርሻ አካላት ወይይት ላይ የተገኙት የጨርቃ ጨርቅ ፌዴሬሽን ተወካይ አቶ ተስፋዬ አብዲሳ ‘’ከንፈር ለማስመጠጥ አይደለም፤ የሚከፈላቸው ደመወዝ ለኑሮ ስለማይበቃቸው ማታ ማታ ከሆቴሎች ተመላሽ ምግቦችን ይዘው የሚገቡ እንዳሉም በጥናት አረጋግጠናል’’ ብለዋል፡፡
በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ተቀጥረው የሚሰሩ ስራተኞች ገቢ እንዲሻሻል ለማድረግ ዝቅተኛ ደመወዝ ወለል ማፅደቅ አንዱ መፍትሄ ነው፤ ያሉት ተወካዩ ‘’በተለይ ሴቶች ክፍያው ዝቅተኛ ስለሆነ በወሲብ ንግድ ላይ የተሰማሩ መኖራቸውን በጥናት አረጋግጠናል’’ ሲሉ አስረድተዋል፡፡
ፌዴሬሽኑ ባካሄደው ጥናት በኢንዱስትሪ ፓርኮች ያሉ አሰሪዎች ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል እንዲወሰን ፈቃደኞች እንዲሆኑ አረጋግጧል ተብሏል፡፡
Comments
00:00