ጥር 12፣ 2017
የተፋሰሶች ከፍተኛ ምክር ቤት በሀገሪቱ የሚከናወኑ ውሃና ውሃ ነክ ፕሮጀክቶች ላይ የጋራ ውሳኔ ለመስጠት ይረዳል ተባለ፡፡
ይህን ያለው የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ነው፡፡
ሚኒስቴሩ በሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የውሃ መስኖና ቆላማ አካባቢዎች ቋሚ ኮሚቴ በተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደርና ማስፈፀሚያ የተፋሰሶች ከፍተኛ ምክር ቤት ማቋቋሚያ አዋጅ ላይ ተወያይቷል፡፡
የተፋሰሶች ከፍተኛ ምክር ቤት ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደሆነ የተነገረ ሲሆን ሰብሳቢው ደግሞ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሆናሉ ተብሏል፡፡
በአገሪቱ የሚከናወኑ ውሃና ውሃ ፕሮጀክቶች ላይ የጋራ ውሳኔ እንዲሰጥ ይረዳል የተባለው የተፋሰሶች ምክር ቤት 17 አባላት እንዳሉት እየተነገረ ሲሆን የተፋሰሶች መጠንም 12 ናቸው ተብሏል፡፡
ያሬድ እንዳሻው
Comments