ግንቦት 26 2017
በቡና ላኪነት ለመሰማራት 15 ሚሊዮን ብር ካፒታል ማስያዝ ሊጠይቅ ነው፡፡
ከዚህ ቀደም የቡና ላኪነትን የብቃት ማረጋገጫ ለማግኘት ይጠየቅ የነረበው የ1.5 ሚሊዮን ብር በ10 እጥፍ እንዲያድግ የተደረገው ዘርፉ በእውቀትና የተሻለ አቅም ባላቸው ሰዎች እንዲያዝ በማስፈለጉ ነው ተብሏል፡፡
ከዚህ ቀደም በቡና ላኪነት የብቃት ማረጋገጫ ለማግኘት ይጠየቅ የነበረው ካፒታል 1.5 ሚሊየን ብር ነበር፤ ይህ ገንዘብ አሁን በአስር እጥፍ እንዲያግ በኢትዮጵያ ቡና ሻይ ባለስልጣን ማሻሻያ መቅረቡ ተሰምቷል።
የሚጠየቀው ካፒታል አነስተኛ ሆኖ በመቆየቱ አትራፊ ነው በሚል ብቻ ብዙዎች የሚገቡበት ዘርፍ ሆኖ ቆይቷል የሚሉት የኢትዮጵያ ቡና ማህበር ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ግዛት ወርቁ ናቸው።
ይሄ ደግሞ እዚሁ ሀገር ቤት በአቅራቢ እና ላኪዎች እንዲሁም ላኪዎች እና የውጭ ገዥዎች መካከል ችግሮች እንዲፈጠሩ ሲያደርግ መቆየቱን ተናግረዋል።
#የቡና_ንግድ ሰዎች የተወሰነ ገንዘብ በአንድ አጋጣሚ ስላገኙ ብቻ የሚገቡበት ሊሆን አይገባም የሚሉት ስራ አስኪያጁ፤ ስለ ዋጋው፣ ጥራቱ እና የአዘገጃጀት ሂደቱ ማወቅ ወሳኝ እንደሆነ ያክላሉ።
Comments