00:00
ሐምሌ 30፣2016
በቅርቡ ሳምንት የመሬት መንሸራት አደጋ ከደረሰባቸው አካባቢዎች አንዱ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል አንዱ ነው፡፡
በከፋ ዞን ባጋጠሙ የመሬት ናዳ አደጋ ለተፈናቀሉና ቤታቸው ለፈረሰባቸው 120 አባዎራዎች ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት እየተሰራ ነው ተብሏል፡፡
በአደጋው 5 ሰዎች ህይወታቸው እንዳለፈ እና በአጠቃላይ 340 የሚሆኑ ሰዎች መፈናቀላቸውን ሰምተናል፡፡
እነዚህ የተፈናቀሉ ሰዎችን በዘላቂነት ለማቀቀም የክልሉ ምክር ቤት የመከረበት መሆኑን እና ከስጋት ነጻ የሆነ አካባቢ ላይ ማስፈር የሚለው ላይ መወያየታቸው ተነግሯል፡፡
Comments
00:00