ነሀሴ 15 2017
የግብአት እጥረት የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽ ዘርፍ ዋነኛው ፈተና ሆኖ በተደጋጋሚ ይነሳል።
ሲሚንቶ፣ ብረት፣ እምነበረድ ወዘተ ማግኘት ከብዷቸው ለሠራተኞቻቸው እንኳን ደመወዝ መከፈል የተቸገሩ ተቋራጮች ብዙ እንደሆኑ ሠምተናል።
ሲሚንቶን ብቻ ብናነሳ እስከ ቅርብ ጊዜ ዓመታዊ ፍላጎቱ 20 ሚሊየን ቶን ሆኖ ሳለ አቅርቦቱ ግን ከ 7 ሚሊየን ቶን ያልበለጠ ነበር።
በርግጥ በቀን 150 ኩንታል የማምረት አቅም ያለው የለሚ ሲሚንቶ ፋብሪካ ባለፈው መስከረም ወር ተመርቆ ጥር ላይ ፤ ምርት ለገበያ ማቅረብ ከጀመረ በኋላ ይህ የአቅርቦትና ፍላጎት ክፍተት መጥበቡ ተነግሯል።
ፋብሪካው ስድስት ወራት ጊዜ ብቻ ከ12 ሚሊየን ኩንታል በላይ ሲሚንቶ ለገበያ አቅርቧል ተብሏል።
ሲሚንቶ ላይ የነበረው ችግር የምርትና አቅርቦት ጉዳይ ብቻ እንዳልሆነ የሚናገረው የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር በበኩሉ ገበያውም ክፍተት እንደነበረበት ጠቅሷል።
በሀገር ውስጥ እጥረት እያለ በህገ ወጥ መንገድ ወደ ውጪ ሁሉ ይላክ እንደነበር የሚኒስቴሩ የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ ኢትዮጵያ በዴቻ ተናግረዋል።
Comments