በሱዳን የቀጠለው ጦርነትን በመሸሽ፤ የሱዳን ዜጎች በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በኩል ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸውን ቀጥለዋል ተብሏል
TRACK

በሱዳን የቀጠለው ጦርነትን በመሸሽ፤ የሱዳን ዜጎች በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በኩል ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸውን ቀጥለዋል ተብሏል

00:00

በሱዳን ጦርነት ምክንያት የተፈናቀሉ እና ከሌላም የአፍሪካ ሀገራት መጥተው በቤኒሻንጉል ጉሙዝ በኩል ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ስደተኞች ቁጥር ከ107,000 ተሻግሯል ተባለ፡፡

በሱዳን የቀጠለው ጦርነትን በመሸሽ፤ የሱዳን ዜጎች በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በኩል ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸውን ቀጥለዋል ተብሏል፡፡

ወደ ክልሉ የሚገቡ ስደተኞች የሚበዙት የሱዳኑ ጦርነት ያፈናቀላቸው ይሁኑ እንጂ የሌሎች አፍርካ ሀገራት ዜጎችም እንዳሉበት ሰምተናል፡፡

በዚህም በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በኩል ብቻ ያሉ ከሌላ ሀገራት የመጡ ስደተኞች ቁጥር ቁጥር 107,222 መሆኑን ክልሉ ነግሮናል፡፡

እነዚህ ስደተኞች ሸርኮሌ፣ ኩርሙክ፣ ባምባሲ እና ኡራ በተባሉ አራት የስደተኛ መጠለያ ጣቢያዎች እንደሚገኙም ሰምተናል፡፡

ለመሆኑ እነዚህ ቁጥራቸው እየጨመረ የመጣው የውጭ ሀገራት ስደተኞች ክልሉ እንዴት እያስተናገዳቸው ነው የደህንነታቸው ጉዳይስ?

ማንያዘዋል ጌታሁን ያሰናዳውን በንጋቱ ሙሉ

Comments

00:00