ታህሣስ 2፣2017
በአቪዬሽን ዘርፍ ዘለግ ያሉ ዓመታት በማስቆጠር በአፍሪካም ከዘርፉ ዓለም አቀፍ ማህበር መስራቾች ቀዳሚ የሆነችው ኢትዮጵያ ኢንዱስትሪው አሁን ላይ የደረሰበትን ዘመናዊ የአሰራር ሥርዓቶች ብትተገብር በብዙ ታተርፋለች ተባለ፡፡
ዓለም አቀፉ የአቪኤሽን ማህበር ሲመሠረት ፈራሚ ከነበሩ ሶስት የአፍሪካ ሀገራት አንዷ የሆነችው ኢትዮጵያ በዘርፍ ያላት ታሪክ ግዙፍ እንደሆነ ይነገራል፡፡
ነገር ግን ዘርፉ ያስቆጠረውን እድሜ ያህል ከሚመጡ አዳዲስ አሰራሮችና ልምዶች ጋር አብሮ መሄድ እንደሚገባው ተነግሯል።
የኢትዮጵያ ሲቪል አቪኤሽን ከተመሠረተ ጀምሮ 80 ዓመታት አስቆጥሯል፤ በእነዚህ ዓመታት በርካታ ለውጦች መከወናቸውንና ሀገሪቱ ለአቪዬሽን ኢንዱስትሪው በአፍሪካ ጭምር አስተዋጽኦዋ ከፍ ያለ እንደነበር የሚናገሩት የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ዋና ስራ አስፈጻሚው አቶ ጌታቸው መንግስቴ ናቸው፡፡
እየተለወጠ ከመጣው ዓለም እና የቴክኖሎጂ ፈጠራ ጋር ለመራመድ ጊዜውን የሚመጥን አሰራር መከተል ላይ በማተኮር ለመስራትና የአቪዬሽን ኢንዱስትሪውን ከአፍሪካ አልፎ በዓለም ተወዳዳሪ ለማድረግ መስራት ይጠበቅብናል ሲሉ አቶ ጌታቸው ተናግረዋል።
Comments