ሰኔ 13፣ 2016  በመጠናቀቅ ላይ ያለው የታላቁ ህዳሴ ግድብ በጉባ አካባቢ ያለውን ሞቃት የአየር ጠባይ እየቀየረው መጥቷል ተባለ፡፡
TRACK

ሰኔ 13፣ 2016 በመጠናቀቅ ላይ ያለው የታላቁ ህዳሴ ግድብ በጉባ አካባቢ ያለውን ሞቃት የአየር ጠባይ እየቀየረው መጥቷል ተባለ፡፡

00:00

ሰኔ 13፣ 2016

በመጠናቀቅ ላይ ያለው የታላቁ ህዳሴ ግድብ በጉባ አካባቢ ያለውን ሞቃት የአየር ጠባይ እየቀየረው መጥቷል ተባለ፡፡

በከፍተኛ የሙቀት መጠን የሚታወቀው የህዳሴ ግድብ እየተገነባበት ያለው በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ የሚገኘው የጉባ አካባቢ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የአየር ጠባዩ እየተቀየረ፣ የነበረው ከባድ ሙቀት መቀነስ አሳይቷል ተብሏል፡፡

ይህ የተባለው ከሰሞኑ በግድቡ ግንባታ ወቅት መገናኛ ብዙሃን የነበራቸውን ሚና በተመለከተ ውይይት በተደረገበት ወቅት ነው፡፡

በዚህም ወቅት የግድቡ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሄራዊ ምክር ቤት እንዳለው በግድቡ ስራ ምክንያት የጉባ አካባቢ ስነ ምህዳር ተቀይሯል፤ ምድረ በዳ የነበረው ስፍራው ለኑሮ ምቹ ወደ መሆን እየተሸጋገረ፤ አንዳንድ ጊዜም ለመተንፈስ እንኳን አስቸጋሪ የነበረው የሙቀት መጠን እተስተካከለ ነው ተብሏል፡፡

Comments

00:00