አንበሳ ኢንሹራንስ በሜትር ታክሲ ለሚጓዙ ሰዎችና ሾፌሮች የጉዞ ደህንነት ዋስትና መስጠት ጀመረ፡፡
TRACK

አንበሳ ኢንሹራንስ በሜትር ታክሲ ለሚጓዙ ሰዎችና ሾፌሮች የጉዞ ደህንነት ዋስትና መስጠት ጀመረ፡፡

00:00

የካቲት 26 2017

አንበሳ ኢንሹራንስ በሜትር ታክሲ ለሚጓዙ ሰዎችና ሾፌሮች የጉዞ ደህንነት ዋስትና መስጠት ጀመረ፡፡

ኩንባያው በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ነው የተባለለትን ይህን የጉዞ ደህንነት ዋስትና መስጠት የጀመረው ሊትል ኢትዮጵያ የሜትር ታክሲ ደንበኞች እና አሽከርካሪዎች መሆኑንን ተናግሯል፡፡

ሁለቱ ኩባንያዎችም ለስምንት ወራት ሲያደርጉት የነበረውን ንግግር አጠናቀው በትናንትናው እለት አብሮ ለመስራት የሚያስችለው ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

አንድ በሊትል ኢትዮጵያ ሜትር ታክሲ አቅራቢ ድርጅት አማካኝነት ጉዞ የሚያደርግ ሰው አደጋ ቢደርስበት ዋስትና እንዲያገኝ ከጉዞ ዋጋ በተጨማሪ 15 ብር ይከፍላል፡፡

በዚህም ጉዳት ካጋጠመ እስከ 1 ሚሊዮን ብር ካሣ የኢንሹራንስ ኩባንያው ይከፍላል ተብሏል፡፡

የሊትል ኢትዮጵያ ሜትር ታክሲ አቅራቢ ኩባንያ መርጠው የሚጓዙ ሁሉ ለአንድ ጉዞ የሚከፈለው ተጨማሪ 15 ብር ከፍለው ዋስትና የማግኘት ግዴታ ውስጥ አይገቡም፡፡

Comments

00:00