00:00
ግንቦት 2፣2016
ስራ ፈጣሪዎችን ለማበረታታት ያግዛለ በሚል መመሪያ የወጣለት ስታርት አፕ(Start UP) ተግባር ላይ ለማዋል ብዙ መስራት ይጠይቃል ተባለ፡፡
በተለያዩ መስኮች የሚመነጩ የፈጠራ ሀሳቦችን ወደ ተግባር ለማውረድ መንገድ ያቃናል በሚል እየተወራ ያለ ጉዳይ ነው ሰታርት አፕ፡፡
በተለይ በአሁን ወቀት ለሀገር አስፈላጊ እንደሆነ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጀምሮ በተለያዩ የዘርፉ አካላት ተደጋግሞ እየተነገረለትም ነው፡፡
የስታርት አፕ ሀሳብ ሲፍታታ፤ ለስራ ፈጣሪዎች የተመች ከባቢን መፍጠር፣ ችግር ፈቺ መስኮች ላይ አተኩሮ መስራት፣ ለዘርፉ የተስማሙ ፖሊሲዎችን አፅድቆ ድጋፍ ማድረግና ተያያዥ ጉዳዮችን ያጠቃልላል፡፡
ይህ ሀሳብ ለዓመታት በተለያዩ አካላት እየተነሳ ቢቆይም ትኩረት ተሰጥቶት ባለመሰራቱ በወጣቶች የመነጩ የስራ ሀሳቦች መሬት ላይ ወርደው ጠቃሚ መሆን ሳይችሉ ቀርተዋል ተብሏል፡፡
ዘርፉ የሚመራበት ህግም በሀገሪቷ አለመኖር ዋነኛው ችግር ሆኖ መቆየቱ ተነግሯል፡፡
መንግስት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሀሳቡ ጠቃሚነት ተረደቻለሁ ብሎ፤ በሚመለከታቸው አካላት የቀረበለትን ዘርፉን እና ተያያዥ መስኮችን የሚደግፉ 11 መመሪያዎችን አስተዋውቋል፡፡
ይሁን እንጂ እነዚህ ይፋ የተደረጉ መመሪያዎች ወደ ተግባር ለማውረድ ገና ብዙ መስራት እንደሚጠይቅ ተነግሯል፡፡
ይህንን የስታርት አፕ ሀሳብን የሚያበረቱ የፖሊሲ ማሻሻያዎችን ሀገሪቱ እንድታደርግ ወትዋች ከነበሩት አካላት መካከል ‘’የኢትዮጵያ ወጣት ስራ ፈጣሪዎች ማህበር’’ የሚጠቀስ ነው፡፡
የማንያዘዋል ጌታሁን ያሰናዳውን በማርታ በቀለ
Comments
00:00