ምጣኔ ሐብት - በማይመስል መንገድ አክስዮን ግዙ፤ ቤት አግኙ የሚሉ ድርጅቶች ጉዳይ
TRACK

ምጣኔ ሐብት - በማይመስል መንገድ አክስዮን ግዙ፤ ቤት አግኙ የሚሉ ድርጅቶች ጉዳይ

00:00

የካቲት 12፣2016

#ምጣኔ_ሐብት

በገበያው ላይ ብዙ ድርጅቶች በማይመስል መንገድ አክስዮን ግዙ ቤት አግኙ እንደሚሉ የኢትዮዽያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ተናግሯል።

ይህን ተከትሎ ባለስልጣኑ አምታች ድርጅቶቹን ወደ ኃላ ሄዶ እንደሚጠይቅና ህዝቡም ቆም ብሎ እንዲያስብ በብርቱ መክሯል

የኢትዮዽያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ታዬ ‘’በኢትዮዽያ ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ እያሉ ብዙ ድርጅቶች ትርፋማ ነን አክስዮን ግዙ በማለት ማስታወቂያ እየነገሩ ነው’’ ብለዋል።

ባለስልጣኑ ‘’ማስታወቂያው ፈፅሞ ከእውነት የራቀ መሆኑን ተረድቻለሁ’’ ብሏል፡፡

የኢትዮዽያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን በዚህ ጉዳይ የሚጠየቀውን ለመጠየቅ የሚሰራውንም ለመስራት ከፋይናንስ ደህንነት መረጃ ማዕከል፣ ከፍትህ ሚኒስቴር፣ ከፌደራል ፖሊስና ከሚመለከታቸው ጋር እየሰራ ነው ተብሏል፡፡

ተህቦ ንጉሴ

#Ethiopia #ShegerWerewoch #የካፒታል_ገበያ_ባለስልጣን #ሪል_ስቴት

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

Comments

00:00