ግንቦት 12 2017
የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ለምርምር ስራ ገንዘብ የሚሰጡ ለጋሾች አጀንዳውንም አብረው ስለሚወስኑ እንደሚቸገር ተናገረ፡፡
ኢንስቲትዩቱ እንደሚለው ለጋሽ ድርጅቶቹ ምርምር እንዲደረግባቸው የሚፈልጓቸው አንዳንድ ጉዳዮች የሀገራችንን ወቅታዊ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ችግሮች የሚያሳዩ አይደሉም፡፡
ኢትዮጵያ ከአጠቃላይ በጀቷ እስከ 0.3 በመቶ የሚሆነውን በዓመት ለምርምር ስራ እንደምትመድብ መረጃዎች ያሳያሉ።
የምርምር ስራው ደግሞ ዩኒቨርሲቲዎችን ጨምሮ በተለያዩ ተቋማት ይከናወናል።
ፖሊሲ ነክ በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ ምርምር እንዲሰራ በህግ ሃላፊነት የተሰጠው ግን ለፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ነው።
ቀደም ሲል የነበሩ ሁለት ተቋማት ማለትም የኢትዮጵያ የልማት ምርምር ኢንስቲትዩት እና የፖሊሲ ጥናት ማዕከል፤
ተዋህደው 2011 ላይ የመሰረቱት የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት አሁን ላይ 73 ተመራማሪዎች እንዳሉት ሠምተናል።
Comments