00:00
መስከረም 14፣2017
በኢትዮጵያ በሚያጋጥም የአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት 35 በመቶ የሚሆኑ ህፃናት ከትምህርት ገበታቸው ይስተጓጎሉ ተባለ፡፡
40 በመቶ የሚሆኑት ህፃናት ደግሞ በውሃ ወለድ በሽታ እና ለተመጣጠነ ምግብ እጥረት እንደሚጋለጡ ጥናት አሳይቷል፡፡
እንደ እ.ኤ.አ ከ2000 እስከ 2022 የተጠኑ ጥናቶች የተጠቀሱትን እውነታዎች አሳይተዋል ተብሏል፡፡
30 በመቶ የሚሆኑት የኢትዮጵያ ህፃናት በሥነ ልቦና ችግር ተፅዕኖ ወይም ጭንቀት ውስጥ እንደሚገቡ ጥናት ያሳያል ይላሉ በ ‘’African Early Childhood Network’’ በተባለ ድርጅት ውስጥ በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ አለም አቀፍ አማካሪ ሆነው የሚሰሩት አቶ ነብያት አየለ፡፡
ከሁለት ዓመታት ወዲህ የተጠና አዲስ ጥናት ባይኖርም አሁን በሀገሪቱ በተለያ አካባቢዎች እየታየ ያለው የተፈጥሮ አደጋ ችግሩ እየከፋ መምጣቱን አመልካች ነው ይላሉ፡፡
በአየር ንብረት ለውጥ እና በሌሎች በተለዩ ችግሮች ህፃናት ላይ የሚደርስን ጉዳት ለማስቀረት ከተማ አስተዳደሩ ከ’’African Early Childhood Network’’ ጋር በመተባበር የአፍሪካ የቀዳማይ ልጅነት ልማት ማዕከል ከዘጠኝ ወራት በፊት ተቋቁሞ ወደ ስራ ገብቷል፡፡
ህፃናት ከፅንስ ጀምሮ ስድስት አመት እስኪሞላቸው ድረስ ማዕከሉ የተለያዩ ድጋፎችን እንደሚያደርግ ተነግሯል፡፡
በፅንስ ወቅት ለእናቶች የሚደረግን የጤና፣ የሥርዓተ ምግብ እና ሌሎች እንክብካቤዎችን ጨምሮ ህፃናቱ ስድስት አመት እስኪሞላቸው ድረስ የሚደረግን ድጋፍ ያካተተ መሆኑ ተነግሮለታል፡፡
ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ለማድመጥ ይህንን ማስፈንጠሪያን ይጫኑ…
ፋሲካ ሙሉወርቅ
Comments
00:00