ሰኔ 24 2017
ለዘመናት የኢትዮጵያን ወጪ ንግድ ሲረብሽ የነበረው ጉዳይ የኮንቴይነር እጥረት፣ የአስተሻሸግ ችግር እና ቅሸባ እንደሆነ ተደጋግሞ ይነሳል።
ይኸው ችግር ኢትዮጵያ በአለም ገበያ የምታቀርባቸውን ምርቶች እንዲወድቁ ወይም እንዲመለሱ አድርጓል።
ይህ በመሆኑም ከወጪ ንግድ የታሰበውን ያህል የውጭ ምንዛሪ ለመለቃቀም ፈትኖ ቆይቷል።
በተለይ በወጪ ንግድ የሚሳተፉ በሙሉ ከፍተኛ የኮንቴነር እጥረት አለ ሲሉ ያማርራሉ።
ከዚህም በላይ የኢትዮጵያ ወጭ ንግድ የውድድር እና ጥራት ችግር እያጋጠመው ምርቱ ሲመለስ ተሰምቷል የሐገርንም ስም በክፉ ሲያስነሳ ቆይቷል።
ይህን እና ተያያዥ የሎጀስቲክስ ችግሮችን ለመፍታት በአንደኛው ጠርዝ የተሰየመው የኢትዮ - ጅቡቲ ምድር ባቡር ከዚህ በኋላ የኮንቴይነር እጥረት አያጋጥመኝም ችግሩንም ለይቻለሁ ብሏል።
Comments