አዋኪ ናቸው የተባሉ፤ እንደ መጠጥ ቤቶች፣ ቁማር ቤቶች እና ሌሎች ከ1,900 በላይ የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ ተወስዷል ተባለ
TRACK

አዋኪ ናቸው የተባሉ፤ እንደ መጠጥ ቤቶች፣ ቁማር ቤቶች እና ሌሎች ከ1,900 በላይ የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ ተወስዷል ተባለ

Avatar

ጥር 16 2017

በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት በአዲስ አበባ ከተማ ባሉ ትምህርት ቤቶች ዙሪያ አዋኪ ናቸው የተባሉ፤ እንደ መጠጥ ቤቶች፣ ቁማር ቤቶች እና ሌሎች ከ1,900 በላይ የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ ተወስዷል ተባለ፡፡

እነዚህ ከ1,900 በላዩ የንግድ ተቋማት በትምህርት ቤቶች ዙሪያ በ500 ሜትር ራዲየስ ላይ የሚገኙ መሆናቸው የተነገረ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ከትምህርት ቤቶቹ ከ200 - 500 ሜትር ራዲየስ ላይ ያሉ 936 የንግድ ተቋማት መታሸጋቸውን ሰምተናል፡፡

ይህንን የሰማነው ከከተማዋ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ነው።

በትምህርት ቤቶች ዙሪያ የነበሩ እና አገልግሎት መስጠት ያቆሙት እነዚህ የንግድ ተቋማት ተለዋጭ ቦታ ተሰጥቷቸው እንዲሰሩ እየተደረገ ነው የተባለ ሲሆን የተቀሩት ደግሞ በዚያው ቦታ ላይ ዘርፍ ቀይረው እንዲሰሩ መደረጉ ተነግሯል።

በተጨማሪም ሸቀጦች ላይ ያለ አግባብ ዋጋ በጨመሩ፣ በህገወጥ መንገድ ምርት ያከማቹ ነጋዴዎችም ተገኝተው ቅጣት ተጥሎባቸዋል ያለው ቢሮው በዚህም በበጀት ዓመቱ 2,000 የሚደርሱትን ቀጥቻለሁ ብሏል።

Comments

Avatar