ታህሳስ 18፣2017
የንብረት ታክስ አዋጅ በህብረተሰቡ ለተደራረበ ግብር እንዲጋለጥ ምክንያት እንዳይሆን ስጋት መፍጠሩ ተነገረ፡፡
የተጋነነ ነው የተባለው የንብረት ታክስ ምጣኔ በታችኛው የህብረተሰብ ክፍል ላይ ጫናውን እንደሚያበረታው በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ተገኝተው በረቂቅ አዋጁ ላይ አስተያታቸውን የሰጡ ተሳታፊዎች ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም ከተማ አስተዳደሮች ያለባቸውን ወጪ መሰረት አድርገው በየዓመቱ የንብረት ግብር ላይ ተመን እንዲያወጡ መፈቀዱ ለመልካም አስተዳደር ችግር ያጋልጣል ተብሏል፡፡
ትዕግስት ዘሪሁን
Comments