''የመጋዘን ደረሰኝ'' አገልግሎት ሥርዓት ይፋ ሆነ
TRACK

''የመጋዘን ደረሰኝ'' አገልግሎት ሥርዓት ይፋ ሆነ

Avatar

ሚያዝያ 16 2017

አርሶ አደሮች ምርታቸውን በማስያዣነት በመጠቀም ከባንኮች ብድር እንዲያገኙ ያስችላል የተባለ የመጋዘን ደረሰኝ አገልግሎት ሥርዓት ይፋ ሆነ፡፡

አሰራሩ በድህረ ምርት ወቅት እንደሚባክን የሚነገረውን ከ30 እስክ 40 በመቶ የሰብል ምርት እንደሚቀንስም ተነግሯል።

በኢትዮጵያ በያመቱ ከ30 እስክ 40 በመቶ የሚሆነው የሰብል ምርት በድህረ ምርት ወቅት እንደሚባክን መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

ለብክነቱ ከሚጠቀሱ ምክንያቶች መካከል ደግሞ ደረጃቸውን የጠበቁ ዘመናዊ መጋዘኖች አለመኖር ይጠቀሳል።

ይህን ችግር ለመፍታት ይረዳል የተባለ #የመጋዘን_ደረሰኝ አገልግሎት ስርአት ይፋ መሆኑን ሠምተናል፡፡

Comments

Avatar