ጥር 22 2017
የእጅ መንሻ ሲቀበሉ ተደርሶባቸዋል የተባሉ 77 የገቢዎች ቢሮ የስራ ሃላፊዎች እስከ ማሰናበት የደረሰ እርምጃ ተወሰደባቸው፡፡
የገቢ አሰባሳቢ ቢሮው ንግድ በህግና ስርዓት እንዲመራ አደርጋለው ብሎ ከወራት በፊት መርካቶን ጨምሮ በመላው በአዲስ አበባ የሚደረጉ ግብይቶች በደረሰኝ እንዲከወኑ ለማድረግ ጠበቅ ያለ ቁጥጥር መጀመሩ ይታወቃል፡፡
በዚህ መሃል ለዚህ ስራ ብሎ ከመደባቸው በርካታ ሰራተኞቹ መካከል 77 ያህሉ ሃላፊነታቸውን ወደ ጎን በመተው ከነጋዴዎቹ ጋር በመደራደር ገንዘብ መቀበላቸውን አረጋግጫለሁ፤ በዚህም ከመካከላቸው 8 አመራሮች ከሃላፊነታቸው ተነስተዋል፣ የተቀሩትም ከደረጃቸው ዝቅ ብለው እንዲሰሩ ተደርጓል፤ የተባረሩም አሉ ያሉን የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተሩ አቶ ሰውነት አየለ ናቸው፡፡
Comments