ወርልድ ቪዥን በ27 የአፍሪካ ሀገራት ስራ ላይ ለሚያውለው ፕሮግራም 1.7 ቢልየን ዶላር መመደቡን ተናገረ
TRACK

ወርልድ ቪዥን በ27 የአፍሪካ ሀገራት ስራ ላይ ለሚያውለው ፕሮግራም 1.7 ቢልየን ዶላር መመደቡን ተናገረ

Avatar

የካቲት 14፣2016

ወርልድ ቪዥን የህጻናት ረሃብ እና ያልተመጣጠነ አመጋገብን ለመቅረፍ ኢትዮጵያን ጨምሮ በ27 የአፍሪካ ሀገራት ስራ ላይ ለሚያውለው ፕሮግራም 1.7 ቢልየን ዶላር መመደቡን ተናገረ፡፡

ይፋ የተደረገው ገንዘብ በምስራቅ፣ በምዕራብ እና በደቡባዊ አፍሪካ ሀገራት ተግባራዊ የሚደረግ ነው ተብሏል።

በወርልድ ቪዥን የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ካርማን ቲል ኢትዮጵያን ጨምሮ በአለም ላይ አሁን የሚታዩ ቀውሶች በህፃናት አማጋገብ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እያሳደሩ ነው ብለዋል፡፡

በተለይ ህፃናት ብቁ ተማሪ እንዲሆኑ የተመጣጠነ ምግብ ዋነኛ መሰረት ነው ያሉ ሲሆን አሁን ለ3 ዓመት የሚተገበረው ፕሮጀክትን በመጠቀም ለጋሽ አካላት እና ባለድርሻ አካል ኢትዮጵያ ውስጥ ህፃናት የምግብ ዋስትናቸው እንዲረጋገጥ ለማድረግ የሚሰራው ስራ እንዲያግዙ እንሰራለን ብለዋል፡፡

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚንስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ በበኩላቸው መንግስት ባለው አቅም ልክ የህፃናት የተመጣጠነ ምግብ እንዲያገኙ ለማድረግ የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ ነው ብለዋል፡፡

ወርልድ ቪዥን እንደ አፍሪካ የሚተገብረው፤ የህፃናት ረሃብና የተመጣጠነ ምግብ እጥረትን ችግር ለመፍታት በሚሰራው ስራ የኢትዮጵያ መንግስት የተጠቃሚዎችን መለየት ላይ አብሮ ይሰራል ብለዋል፡፡

፡፡

በረከት አካሉ

#Ethiopia #ShegerWerewoch #EEA #የኢትዮጵያ_ኢኮኖሚክስ_ባለያሞዎች_ማህበር

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

Comments

Avatar