የካቲት 14፣2016 - የገበያ ቅኝት - በሀገር ቤት ተመርቶ የሚቀርበው ጤፍ ለምን በዚህ ልክ ተወደደ?
TRACK

የካቲት 14፣2016 - የገበያ ቅኝት - በሀገር ቤት ተመርቶ የሚቀርበው ጤፍ ለምን በዚህ ልክ ተወደደ?

Avatar

የካቲት 14፣2016

በአዲስ አበባ ከተማ የሸቀጦች ዋጋ መናር የነዋሪውን ህይወት እንደፈተነው ተደጋግሞ ይነገራል።

ከቅርብ ጊዝ ወዲህ ጤፍን ጨምሮ ሌሎች ሸቀጦች በአንድ ጀንበር ዋጋቸው ከፍ ማለቱ የሚታወቅ ነው፡፡

ነገር ግን ከሰሞኑ የሽንኩርት እና የቲማቲም ዋጋ እቀነሰ ቢሆንም የጤፍ ዋጋ ጨምሯል፡፡

ጤፍ ከወራት በፊትም ከስድስት ሺህ ብር ወደ አስራ ሁለት ሺህ፣ አስራ ሶስት ሺህ እና አስራ አራት ሺህ ብር በአንድ ጊዜ የዋጋ ጭማሪ አሳይቷል።

ሸገር በአንዳንድ ወፍጮ ቤቶች ተዘዋውሮ ጤፍ ሲገበያይ የሰነበተበትን ዋጋ ተመልክቷል፡፡

በዚህም በየደረጃው ከ135 ብር እስከ 145 ብር በኪሎ እየተሸጠ መሆኑን አይቷል፡፡

እዚሁ በሀገር ቤት ተመርቶ የሚቀርበው ጤፍ ለምን በዚህ ልክ ተወደደ?

ለምንስ የአቅርቦት እና የፍላጎት አለመጣጣም ሊያጋጥም ቻለ?

ሸገር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮን ጠይቋል።

ፋሲካ ሙሉወርቅ

#Ethiopia #ShegerWerewoch #ሽንኩርት #ቲማቲም #የጤፍ_ዋጋ

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

Comments

Avatar