TRACK
የካቲት 11/2018 መንግስት የዘይት ፍላጎትን ሀገር ውስጥ ለሟሟላት በሚል በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር ለባለሃብቶች እንዲቀርብ ማድረጉ ይታሰዋል፡፡
የካቲት 11/2018
መንግስት የዘይት ፍላጎትን ሀገር ውስጥ ለሟሟላት በሚል በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር ለባለሃብቶች እንዲቀርብ ማድረጉ ይታሰዋል፡፡
እነዚህ ድጋፍ የተደረገላቸው ፋብሪካዎች ሀገር ውስጥ ያለውን የዘይት ፍላጎት በተወሰነ ደረጃ ፍላጎት ያሟላሉ ገበያውንም ያረጋጋሉ ተብሎም ተስፋ ተጥሎባቸው ነበር፡፡
ታዲያ ይህ ከምን ደረሰ ድጋፍ ያገኙት የዘይት ፋብሪካዎች አሁን ምን ደረጃ ላይ ናቸው የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩን አቶ መላኩ አለበልን ጠይቀናቸዋል፡፡
አቶ መላኩ ከዚህ ቀደም በየአካባቢው ዘይት በመጭመቅ ይሰሩ የነበሩ አምራቾች ገበያ ውስጥ መወዳደር ስላቃታቸው አሁን ከዘርፉ ወጥተዋል ብለዋል፡፡
መንግስት ከዚህ ቀደም ድጋፍ ያደረገላቸው የዘይት ፋብሪካዎች አሁን በምርት ላይ ናቸው ከባለፈው ሰኔ ጀምሮ የማምረቻ ግብአት እጥረት ገጥሟቸው ነበር አሁን አዲስ ምርት ስለገባ ይህ ችግር ተፈቶላቸዋል ሲሉም ነግረውናል፡፡
Comments