ፈቃድ ያላቸው የመገናኛ ብዙኃን አጠቃላይ ብዛት 292 እንደደረሱ ተነገረ
TRACK

ፈቃድ ያላቸው የመገናኛ ብዙኃን አጠቃላይ ብዛት 292 እንደደረሱ ተነገረ

Avatar

ሚያዝያ 14 2017

በኢትዮጵያ በበይነ መረብ አማካኝነት መረጃን ከሚያስተላለፉት መካከል 65 ያህሉ ህጋዊ ፈቃድ እንዳገኙ ተነገረ፡፡

በዚህም በኢትዮጵያ ፈቃድ ያላቸው የመገናኛ ብዙኃን አጠቃላይ ብዛት 292 እንደደረሱ ሰምተናል፡፡

የመገናኛ ብዙኃኑ የሚመዘገቡበት ዘርፍም ወደ አስር አድጓል ተብሏል፡፡

ከእነዚህ ዘርፎችም፣ የህዝብ፣ የማህበረሰብ፣ የሀይማኖት፣ የንግድ፣ የበይነ መረብ፣ የክፍያ(እንደ ዲኤስ ቲቪ ያሉ) እና የትምህርት የመገናኛ ብዙሃን እንደሚገኙበት ተጠቅሷል፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን ባለስልጣን አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ተከትለው እየመጡ ያሉ የመገናኛ ብዙሀን ዘርፎችን ወደ አሰራሬ አስገብቼ ለመመዝገብ እየበረታሁ ነው ብሏል፡፡

ማንያዘዋል ጌታሁን ያዘጋጀውን በወንድሙ ሀይሉ

Comments

Avatar