TRACK
ኢትዮጵያ የምታስገባው ነዳጅ የጥራት ፍተሻውን ለማድረግ የሚያስችላት ላብራቶሪ ስሌላት ናሙናው ወደ ኬንያ እና ሌሎች ሀገራት እንደሚላክ ሠምተናል።
ግንቦት 28 2017
ኢትዮጵያ በጅቡቲ በኩል የምታስገባው ነዳጅ፤ ጅቡቲ በሚገኘው ሆራይዘን የነዳጅ ማጠራቀሚያ ዴፖ ነው።
ነዳጁ ከመርከቦች ወደ ዴፖው ከመራፉ በፊት ግን የጥራት ፍተሻ እንደሚደረግለት ተነግሯል።
ኢትዮጵያ የጥራት ፍተሻውን ለማድረግ የሚያስችላት ላብራቶሪ ስሌላት ናሙናው ወደ #ኬንያ እና ሌሎች ሀገራት እንደሚላክ ሠምተናል።
የነዳጁ ጥራት ተረጋግጦ እስኪመጣ አንድ መርከብ አንድ ቀን ሲቆም ኢትዮጵያ እስከ 25 ሺህ ዶላር ትከፍላለች ተብሏል።
አሁን የነዳጅ ጥራት ፍተሻው የሚደረግበት ላብራቶሪ ድሬደዋ ላይ እየተገነባ እንደሚገኝ በአፍሪካ የንግድና ሊጂስቲክስ ላይ አትኩሮ የሚሰራው እና ትሬድ ማርክ አፍሪካ የተሰኘው መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት የኢትዮጵያ ተወካይ አቶ እውነቱ ታዬ ነግረውናል።
ከኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ጋር በመተባበር እየተገነባ ያለው ይህ ላቦራቶሪ 1 ነጥብ 6 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር የተመደበለት ነው ተብሏል።
Comments