TRACK
በቅርቡ ሹመት ለተሰጣቸው ቆንስላዎች፣ ዲፕሎማቶችና እጩ ምባሳደሮች ዛሬ በስካይ ላይት ሆቴል ስልጠና መስጠት መጀመሩ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ተናገረ
ሐምሌ 4፣ 2016
የኢትዮጵያ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር በተለያዩ አለማት ኢትዮጵያን ለሚወክሉ እና በቅርቡ ሹመት ለተሰጣቸው ቆንስላዎች፣ ዲፕሎማቶችና እጩ ምባሳደሮች ዛሬ በስካይ ላይት ሆቴል ስልጠና መስጠት መጀመሩ ተናገረ፡፡
የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ በቅርቡ ለተሾሙ የኢትዮጵያ ወኪሎች ስልጠና መጀመሩን ምክንያት በማድረግ ባደረጉት ንግግር በእውቀትና በጥበብ ያልተያዘ ዲፕሎማሲ የሀገርን ጥቅም ማስከበር ስለማይችል የሚሰጡ ስልጠናዎች አስፈላጊ ናቸው ብለዋል፡፡
ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሐምሌ 20 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ በሚዘልቀው የኢትዮጵያ ወኪሎች ስልጠና የተለያዩ የዲፕሎማሲ ክዕሎትን ያሳድጋል የተባሉ የስልጠና መርሃ ግብሮች መዘጋጀታቸውም አምባሳደር ታዬ ተናግረዋል፡፡
Comments