በኢትዮጵያ ከሚወለዱ ህፃናት ምን ያህሉ ይሞታሉ?
TRACK

በኢትዮጵያ ከሚወለዱ ህፃናት ምን ያህሉ ይሞታሉ?

00:00

ጥቅምት 8፣2017

በኢትዮጵያ ከሚወለዱ ህፃናት ምን ያህሉ ይሞታሉ?

ከሚወልዱ እናቶችስ ሞት የሚያጋጥማቸው ምን ያህሎቹ ናቸው?

እነዚህንና ሌላውም በቁጥር ለማወቅ እየተጠኑ እንደሆነ ተነግሯል፡፡

ወትሮውንም ቢሆን በወሊድ ወቅት የሚከሰት የእናቶችና ህፃናት ሞት ከፍ ብሎ በሚታይባት ኢትዮጵያ አሁን ያለው ግጭትና መፈናቀል ተጨምሮበት ጥናቱ ምን ውጤት ይዞ ይመጣ ይሆን? የሚለው ተጠባቂ ሆኗል፡፡

‘’የኢትዮጵያ የስነ ህዝብና ጤና ጥናት’’ በሚል እነዚህንና ሌሎችንም ጤና ነክ ጉዳዮች በዝርዝር የሚጠኑበት ጥናት በየ5 ዓመቱ የሚካሄድ ነው፡፡

በስታቲስቲክስ አገልግሎት የሚከወነው ጥናቱ ለመጨረሻ ጊዜ የተደረገው የዛሬ 5 ዓመት ነው፡፡

የዘንድሮው ደግሞ ካለፈው ሐምሌ ወር 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከወነ ይገኛል፡፡

Comments

00:00