መጋቢት 3 2017
ከመድሃኒት አቅርቦት ጋር ተያይዞ 80 በመቶ የሚሆኑት የጤና ተቋማት በብድር እንደሚገዙ የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ተናገረ፡፡
የመድኃኒት አቅርቦት ችግር ከጊዜ ወደጊዜ እንዳይሻሻል ካደረጉት መካከል አንዱ የብድር ጉዳይ ቢሆንም የተቋማት አለመናበብ ግጭቶችና ሌሎችም የራሳቸውን ተጽዕኖ እንዳሳደሩ ተቋሙ አስረድቷል፡፡
ይህ በጥናት መረጋገጡን የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ ተናግረዋል፡፡
ለማህበረሰብ የጤና መድህን አገልግሎት ከ 50 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ቢመዘገቡ የመድኃኒት ፍላጎትና አቅርቦት ሊመጣጠን እንዳልቻለም ተነስቷል፡፡
የጤና ተቋማቱ የወሰዱትን ብድር በወቅቱ ባለመመለሳቸው የመድኃኒት አቅርቦቱ ላይ ጫና ማሳደሩንና መድሃኒቱን መልሶ ለመግዛት እንዳልተቻለ ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡
Comments