የዋጋ ንረቱ፣ ስራ አጥነቱ እየፈተነው ያለው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ መፍትሄው ምን ይሆን?
TRACK

የዋጋ ንረቱ፣ ስራ አጥነቱ እየፈተነው ያለው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ መፍትሄው ምን ይሆን?

Avatar

ጥቅምት 19፣2017

የዋጋው ግሽበት፣ የእርስ በእርስ ግጭት፣ የሰላም እጦትና ከፍተኛ የስራ አጥ ቁጥር በኢትጵያ ያሉ ችግሮች መሆናቸው ተደጋግሞ ይነገራል፡፡

በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ያሉ አለመግባባቶችና ግጭቶች አርሶ አደሩ መሬቱን አርሶ፣ ዘርቶ እንዳያመርት፣ ያመረተውን ይዞ ለገበያ እንዳያቀርብ እንቅፋት ሆኗል ተብሏል፡፡

የዋጋ ንረቱ፣ ስራ አጥነቱ፣ እየፈተነው ያለው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ መፍትሄው ምን ይሆን?

በጉዳዩ ላይ የኢኮኖሚ ባለሞያውን አቶ ክቡር ገናን ጠይቀናቸዋል።

እሳቸው በሀገሪቱ ያሉ የፖለቲካ አለመረጋጋቶች ካልተፈቱ የታሰበውን የኢኮኖሚ እድገት ይመጣል የሚል እምነት እንደሌላቸው አስረድተዋል፡፡

በፌዴራል መንግስትና በህወሃት መካከል የተደረገው ጦርነትም የሀገሪቱን ልማት ብዙ ዓመታት ወደ ኋላ የጎተተ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

ባለሙያው አሁንም እዚህም እዚያም የሚታዩ ግጭቶችን መፍታት በኢኮኖሚው ላይ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት እንደሚረዳ አስረድተዋል፡፡

Comments

Avatar