በጅቡቲ ያለው ሙቀት ከፍተኛ በመሆኑ ከኢትዮጵያ ለጭነት የሚሄዱ አሽከርካሪዎች ለሞት ጭምር እየተዳረጉ  መሆኑ ተነግሯል
TRACK

በጅቡቲ ያለው ሙቀት ከፍተኛ በመሆኑ ከኢትዮጵያ ለጭነት የሚሄዱ አሽከርካሪዎች ለሞት ጭምር እየተዳረጉ መሆኑ ተነግሯል

00:00

ነሐሴ 17፣2016

በጅቡቲ ያለው ሙቀት ከፍተኛ በመሆኑ ከኢትዮጵያ ለጭነት የሚሄዱ አሽከርካሪዎች ለሞት ጭምር እየተዳረጉ መሆኑ ተነግሯል፡፡

ባለፉት ሁለት ወራት ብቻም 5 የከባድ ጭነት መከና አሽከርካሪዎች፤ በመኪናቸው ውስጥ እና ከመኪናቸው ስር ሞተው ተገኝተዋል ተብሏል፡፡

የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማህበር፤ ለአሽከርካሪዎቹ በሙቀት መሞት ባለሀብቶችን ተጠያቂ አድርጓል፡፡

የማህበሩ ስራ አስኪያጅ ሰለሞን ዘውዱ ጉዳዩን ሲያብራሩም፤ ‘’አሽከርካሪዎቹ ለሞት የሚዳረጉት የጭነት ወረፋቸው ሳይደርስ ባለሀብቶቹ ወደ ጀቡቲ እንዲሄዱ ስለሚያደርጓቸው ነው’’ ብለዋል፡፡

በመኪና በባለንብረቶች የተቋቋመው የኢትዮጵያ ትራንስፖርት አሰሪዎች ማህበር በበኩሉ፤ ተሽከርካራች በጅቡቲ ወደብ እስከ 6 ቀን ሊቆዩ ይችላሉ ይህ የሚሆነውም በአብዛኛውም ጊዜ ኮንቴይነር ሳይቀርብ ሲቀር እንደሆነ ተናግሯል፡፡

የማህበሩ የህዝብ ግኑኝነት ሀላፊ ደጀኔ ሎጬ፤ ‘’በጀቡቲ ወደብ ያለው ሙቀት ለአሽከርካሪዎች ከባድ እንደሆነ እንረዳለን፣ ተሽከርካሪዎች እዛ ብዙ ቀናት በቆዩ ቁጥር ባለሀብቱም ወጪ ሊያስወጡ የሚችሉ አጋጣሚዎችም ሊኖሩ ይችላሉ፤ በዚህም ባለሀብቱም መኪኖቹ እዚያ ሄደው እንዲቆሙ አይፈልጉምም’’ ብለውናል፡፡

ማንያዘዋል ጌታሁን ያሰናዳውን በፋሲካ ሙሉወርቅ

Comments

00:00