መጋቢት 24 2017
በመንግስት አገልግሎት ሰጭዎች የሚጠይቁትን የአገልግሎት ክፍያ በመቶዎች እጥፍ ማሳደጋቸው፤ ደንብ ለማስከበር በሚል የሚወጡ ደንቦች ህግ ተላልፈው ተገኝተዋል ያሏቸውን እስከ 1 ሚሊዮን ብር የሚያስከፍሉ ድንጋጌዎችን ስራ ላይ ማዋላቸው ይታወቃል፡፡
የመንግስት ገቢም ለማሳደግ ያለሙ እንዲህ ያሉ ህጎች በተለይ ደሞዝተኛን ለከፍተኛ ጫና ዳርገውታል ይባላል፡፡
ይቋቋማል ለተባለው ለአደጋ ፈንድ ደሞዝተኞች ከደሞዛቸው እንዲያዋጡ የሚደነገገውን ህግ መነሻ አድርገን ከህግ አወጣጥ መርህ አንፃር እንዴት ይታያል የሚለውን ጠይቀናል፡፡
ደመወዝኛው በየወሩ የሚቆቀርጥበት;-
- እስከ 35% የገቢ ግብር
- 7 % የጡረታ
- 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ (የሞባይል ባንኪንግን ጨምሮ የተለያዩ አገልግሎቶችን ለማግኘትና ምርቶችን ሲሸምት የሚቆርጥበት)
- እጁ ላይ የሚቀረው ከደሞዙ 43 በመቶ ብቻ ይሆናል
- ከቀሪው ላይ ደግሞ የዋጋ ግሽበቱ 15 በመቶውን (በመንግስት መረጃ መሰረት) ይወስድበታል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ከደሞዝተኛው ላይ እንዲቆረጥበት የሚደነግግ ህግ መውጣቱ “ለሰዎች ከፍተኛ ጥቅም ትንሽ ችግር የሚሰጥ ከሚለው” የህግ አወጣጥ ሳይንስ የሚቃረን እና የሰዎችን ችግር የሚያበዛ ነው ተብሏል፡፡
በጉዳዩ ላይ የህግ አወጣጥ ዘዴ መምህር አነጋገረንበታል፡፡
ሙሉ ዘገባወን….
ትዕግስት ዘሪሁን
Comments