ሐምሌ 26፣2016
የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ አደጋዎች በኢትዮጵያ ደጋግመው እያጋጠሙ ነው፡፡
በእዚህ ምክንያት ወረርሽኞች ተቀስቅሰው ችግሩ እንዳይበረታ ምን እየተሰራ ነው?
በዚህም #የኢትዮጵያ_ህብረተሰብ_ጤና_ኢንስቲትዩት አስቀድሞ የዳሰሳ ጥናት እንደሚያደርግ የተናገረ ሲሆን ይህ የዳሰሳ ጥናት የተጋላጭነትና የጤና ስጋቶችን ለመለየት እንደሚረዳው ሰምተናል፡፡
ኢንስቲትዩቱ እንዲህ አይነት አደጋዎች ሲከሰቱ የዳሰሳ ጥናቶቹ ለመከላከል፣ የዝግጅት ስተራ ለመከወን እንዲሁም ለምላሽና ለመልሶ ማቋቋም ለመተግበር ይረዳኛል ብሏል፡፡
ይህን ሁሉ ሳደርግ ግን ብቻዬን ሳይሆን ከኢትዮጵያ ሜትሮሎጂ ኢንስቲትዩት፣ ከኢትዮጵያ አደጋ ስጋ አመራር ኮሚሽን ጋር በመሆን የቅድመ መከላከል ስራን እሰራለሁ ብሏል፡፡
ማርታ በቀለ
#ወረርሽኝ #የተፈጥሮ_አደጋ
Comments