የግብርና ሚኒስቴር በተጠናቀቀው 2016 ዓ.ም እሰራዋለሁ ካለው ጉዳይ አንዱ አሲዳማ መሬትን ማከም ነበር
TRACK

የግብርና ሚኒስቴር በተጠናቀቀው 2016 ዓ.ም እሰራዋለሁ ካለው ጉዳይ አንዱ አሲዳማ መሬትን ማከም ነበር

Avatar

መስከረም 6፣2017

የግብርና ሚኒስቴር በተጠናቀቀው 2016 ዓ.ም እሰራዋለሁ ካለው ጉዳይ አንዱ አሲዳማ መሬትን ማከም ነበር፡፡

ኢትዮጵያ ከምታርሰው መሬት ውስጥ 43 ከመቶ ወይም 7 ሚሊዮን ሄክታር የሚሆነው መሬቷ በአሲድ እንደተጠቃ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ተናግሮ ነበር፡፡

ከዚህ ውስጥ 3.1 ሚሊዮን ሄክታር የሚሆነው በጠንካራ አሲዳማነት የተጠቂ አፈር ነው፡፡

መሬቱን ለግብርና ስራ ለማዋል በዓመት 6.2 ሚልየን ኩንታል ማዳበሪያ ጥቅም ላይ የሚውል ሲሆን መሬቱ አሲዳማ በመሆኑና በአግባቡ ስለማይቀበለው 70 ከመቶ የሚሆነው የአፈር ማዳበሪያ ይባክናል ተብሏል።

በዚህም ሀገሪቱ 19 ቢሊዮን ብር በአፈር አሲድ ምክንያት በዓመት ይባክንባታል ሲል የግብርና ሚኒስቴር ተናግሯል።

የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ በአሲዳማ አፈር ምክንያት ኢትዮጵያ ከፍተኛ ምርት ይባክንባታል ሲሉም አስረድተዋል።

አሲዳማ አፈር በአብዛኛው የሚከሰተው በደጋ እና ወይና ደጋ የኢትዮጵያ ክፍል አካባቢ ነው ያሉት ሚንስትሩ ለዚህም ምክንያቱ መሬቱ፤ በዝናብ ስለሚታጠብና በአንዳንድ የአፈር ማዳበርያ አጠቃቀም ተብሏል፡፡

Comments

Avatar