የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በኢትዮጵያ ያሉ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን ለመደገፍ ፍላጎት አለኝ ማለቱ ተነግሯል።
TRACK

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በኢትዮጵያ ያሉ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን ለመደገፍ ፍላጎት አለኝ ማለቱ ተነግሯል።

00:00

የካቲት 8፣2016

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በኢትዮጵያ ያሉ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን ለመደገፍ ፍላጎት አለኝ ማለቱ ተነግሯል።

የድርጅቱ ረዳት ዋና ፀሐፊ ራሚዝ አላክባሮቭ የቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክን አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴና በፓርኩ የሚገኙ ‘’ሱፍሌ’’ እና ‘’ጄጄ’’ ኩባንያዎችን የምርት ሂደት ተዘዋውረው መመልከታቸውን ሠምተናል።

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ የኮርፖሬሽኑ አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴዎች በተለይም በስራ ዕድል ፈጠራ፣ በአካባቢ ጥበቃ፣ በገበያ ትሰስርና ኢንዱስትሪያላይዜሽን ላይ ያተኮረ ገለጻ ለረዳት ዋና ፀሃፊው እንዳደረጉ ተነግሯል፡፡

ረዳት ዋና ፀሃፊው በበኩላቸው ኮርፖሬሽኑ በተለይ ለሀገር በቀል ኩባንያዎች እና ባለሃብቶች የሰጠውን ትኩረት አድንቀዋል ሲሉ የኮርፖሬሽኑ የማርኬቲንግ፣ ቢዝነስ እና ኢንቨስትመንት ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ ዘመን ጁነይዲ ነግረውናል።

ለአርሶ አደሮች የገበያ ትስስር፣ ለወጣቶች እና ሴቶች ደግሞ የስራ ዕድል በመፍጠር በኩል የተሰራው ስራም ጥሩ እንደሆነ መናገራቸውን ከአቶ ዘመን ሠምተናል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ጋር በቅርበት የመስራት ፍላጎት አለው ሲሉ ረዳት ዋና ፀሃፊው ተናግረዋል ተብሏል፡፡

ንጋቱ ረጋሳ ያሰናዳውን በማርታ በቀለ

#Ethiopia #ShegerWerewoch #ለሚ_ኢንዱስትሪ_ፓርክ

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

Comments

00:00