አገልግሎት መስጠት ያቆሙ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶችን የመልሶ ግንባታ እያከናወንኩ ቢሆንም ፈተናዎች ይገጥሙኛል ሲል የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተናገረ
TRACK

አገልግሎት መስጠት ያቆሙ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶችን የመልሶ ግንባታ እያከናወንኩ ቢሆንም ፈተናዎች ይገጥሙኛል ሲል የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተናገረ

00:00

ነሐሴ 15፣2016

በሰላም እጦትም ሆነ በስርቆት ምክንያት አገልግሎት መስጠት ያቆሙ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶችን የመልሶ ግንባታ እያከናወንኩ ቢሆንም ፈተናዎች ይገጥሙኛል ሲል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተናገረ፡፡

በተለያዩ ምክንያቶች ከጥቅም ውጭ የሆኑ መሰረተ ልማቶችን መልሶ የመጠገን ስራ እየከወንኩ ነው ያለው ተቋሙ አገልግሎቱን ወደ ነበረበት ለለመመለስ የማወጣው ወጭ አዳዲስ መሰረተ ልማቶችን ይከውንልኝ ነበር ብሏል፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሚፈጠረው የሰላም እጦት በመሰረተ ልማቶቹ ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል ያሉት የአገልግሎቱ የኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ መላኩ ታዬ በስርቆት ምክንያትም ችግር የደረሰባቸው መሰረተ ልማቶች እንዳሉ ተናግረዋል፡፡

ከአራት እስከ ስድስት ለአመታት አገልግሎት መስጠት ያቆሙ መሰረተ ልማቶች መኖራቸውም የተነገረ ሲሆን እነሱን በመጠገን አገልግሎት እንዲሰጡ የማድረግ ስራ እየተከወነ ነው መሆኑን ዳይሬክተሩ አስረድተዋል፡፡

Comments

00:00