መጪውን የፈረንጆች አዲስ ዓመት እንዲሁም የገና በዓል ወደ ቤተሰቦቻቸው ለሚሄዱ የውጪ ዜጎች በተለይም ለዲኘሎማቲክ ማህበረሰቡ አውደርዕይ መሰናዳቱ ተነገረ
TRACK

መጪውን የፈረንጆች አዲስ ዓመት እንዲሁም የገና በዓል ወደ ቤተሰቦቻቸው ለሚሄዱ የውጪ ዜጎች በተለይም ለዲኘሎማቲክ ማህበረሰቡ አውደርዕይ መሰናዳቱ ተነገረ

Avatar

ህዳር 12 2018

መጪውን የፈረንጆች አዲስ ዓመት እንዲሁም የገና በዓል አስመልክቶ ወደ ቤተሰቦቻቸው ለሚሄዱ የውጪ ሃገር ዜጎች በተለይም ለዲኘሎማቲክ ማህበረሰቡ አውደርዕይ መሰናዳቱ ተነገረ፡፡

ኢትዮጵያን ለዓለም ሀገራት ለማስተዋቅ የተለያዩ ለስጦታ የሚሆኑ ምርቶች ይገኙበታል የተባለው አውደርዕይ የተሰናዳው በሦስት ድርጅቶች ነው ተብሏል፡፡

ኤልቬዜት ኢንተርናሽናል ኤቨንት፣ ዲሊኦፖል ሆቴል፣ እና ሳራ ኔክስት ፋሽን ዲዛይን በጋራ አውደርዕዩን ማሰናዳታቸው ተነግሯል፡፡

የፈረንጆቹ የገና በዓል የተለያዩ ስጦታዎች የሚሰጡበት በመሆኑ ይህንን እድል በመጠቀም ምርቶች እንዲተዋወቁ አውደ ርዕዩ መሰናዳቱን የሳራ ኔክስት ፋሽን ዲዛይን መስራች ሳራ መሀመድ ተናግረዋል፡፡

Comments

Avatar