የነዋሪዎቿም ቁጥር እያሻቀበ የመጣቸው አዲስ አበባ የከተማዋን ስፋት እና የኗሪዎቿን ቁጥር ያህል የሚመጥን የመንገድ መሰረተ ልማት ትፈልጋለች
TRACK

የነዋሪዎቿም ቁጥር እያሻቀበ የመጣቸው አዲስ አበባ የከተማዋን ስፋት እና የኗሪዎቿን ቁጥር ያህል የሚመጥን የመንገድ መሰረተ ልማት ትፈልጋለች

Avatar

ግንቦት 26 2017

በየጊዜው የእሰፋች የነዋሪዎቿም ቁጥር እያሻቀበ የመጣቸው አዲስ አበባ የከተማዋን ስፋት እና የኗሪዎቿን ቁጥር ያህል የሚመጥን የመንገድ መሰረተ ልማት ትፈልጋለች፡፡

ምንም እንኳን ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዝቅተኛ የተሽከርካሪ መጠን ያላት ሀገር ብትሆንም በትራፊክ አደጋ ግን ከፍተኛውን የሞትና የአካል ጉዳት መጠን የምታስተናግድ መሆኑን ሪፖርቶች ያሳያሉ፡፡

ለተሽከርካሪም ይሁን ለእግረኞች የተመቸ የመንገድ መሰረተ ልማቶች መገንባት ደግሞ ይህንን አደጋ በጥፍ እንደሚቀንሰው ይነገራል፤ በአዲስ አበባ መንገዶች ላይ ያለው ግን ከዚህ የተለየ ነው፤ ከአመታት በፊት በዓለም አቀፍ ተቋም የተጠናና የከተማዋን መንገዶች የዳሰሳ ጥናት እንደሚለው ለመንገዶች ከሚሰጠው የኮከብ ደረጃ የአዲስ አበባዎቹ ጥቂቱን ብቻ ነው የሚያሟሉት፡፡

ይህንን ለማሻሻል ባለፉት ዓመታት የተሰሩ የመንገድ ደህንነት እና የመሰረተ ልማት ስራዎች ጥቂት ማሻሻያ አላቸው አሁን ባለው የመንገዶቹ የኮከብ ደረጃ መንገዶች እስከ ሁለት ኮከብ ደርሷል የሚሉት የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ክበበው ሚደቅሳ ናቸው፡፡

በአለም አቀፍ ደረጃ ያለው የመንገድ መሠረተ ልማቶች ግንባታ ምን ይመስላል? በተለይ የእግረኞች ደህንነትን መጠበቅ ላይስ ያለው እውነታው ምን መሳይ ነው ስንል የመንገድ ደህንነት ባለሙያውን አቶ ዮሐንስ ለገሰ አነጋግረናል፤ እርሳቸው በአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የመንገድ ደህንነት ላይ የሚሰራው ዓለም አቀፉ ብሉምበርግ አስተባባሪ ናቸው፡፡

Comments

Avatar