የጥቅምት 7፣2017
ጡረተኞች እና የመንግስት ሰራተኞች የጤና መድህን አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ እየተሰራ ነው ተባለ፡፡ በተለይ ጡረተኞች ቅሬታ ሲያቀርቡ እንደነበር ይታወሳል፡፡
በተደጋጋሚ ጊዜ ጡረተኞች እኛም ገቢያችን ዝቅተኛ በመሆኑ ተጠቃሚ እንሁን ሲሉ ይጠይቃሉ፡፡
ይሁን እና በተያዘው የበጀት ዓመት እንዲመዘገብ እንቅስቃሴ መጀመሩን ከአዲስ አበባ ከተማ የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን ሰምተናል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የጤና መድህን ተጠቃሚ ሆነን መድሃኒት ለመግዛት ወደ ከነማ መድሃኒት ቤቶች ስንሄድ መድሃኒት እያለ የለም እንባላለን ሲሉ ነዋሪዎች ቅሬታ ያነሳሉ፡፡
Comments