በአዲስ አበባ  ከዚህ ቀደም በዲጂታል መላ ያልተመዘገቡ የነዋሪነት መታወቂያ፣ ያገባ፣ ያላገባ አገልግሎቶችን በአብዛኛው መሰጠት ማቆማቸው ተሰማ
TRACK

በአዲስ አበባ ከዚህ ቀደም በዲጂታል መላ ያልተመዘገቡ የነዋሪነት መታወቂያ፣ ያገባ፣ ያላገባ አገልግሎቶችን በአብዛኛው መሰጠት ማቆማቸው ተሰማ

Avatar

ህዳር 25፣2017

በአደስ አበባ ከዚህ ቀደም በዲጂታል መላ ያልተመዘገቡ የነዋሪነት መታወቂያ፣ ያገባ፣ ያላገባ አገልግሎቶችን የሲስተም ችግር በማጋጠሙ በአብዛኛው መሰጠት ማቆማቸው ተሰማ፡፡

አገልግሎቶቹ የቆሙት፤ ተመዝጋቢዎች መዝግቦ አሻራ የሚወስደው ማሽን እክል ስላጋጠመው ነው ተብሏል፡፡

ሆኖም ሙሉ በሙሉ ቆሟል ማለት እንዳልሆነ እና ከዚህ ቀደም በዲጂታል የተመዘገብ የከተማዋ ነዋሪዋች ኤጀንሲው የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ማግኘት እንደሚችሉ ሰምተናል፡፡

የተፈጠረው የሲስተም የመቆራረጥ ችግር ሳምንታትን ያስቆጠረ ሲሆን መንስኤውን እና መፍትሄውን ለመፈለግ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመሆን እየሰራን ነው ሲሉ የአደስ አበባ የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና ዳሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ ነግረውናል፡፡

Comments

Avatar