ጉዳያችን - የከተማ ግብርና
TRACK

ጉዳያችን - የከተማ ግብርና

Avatar

ሰኔ 9 2017

#ጉዳያችን

በከተማ ግብርና ሰበብ የዶሮ እና ከብት እርባታን ወደ ከተማ ማቅረብ ምን አደጋ አለው?

የምርት እድገትን በመጨመር በተመጣጠነ ዋጋ ሰዎች የእንስሳት ተዋፅኦ ምርቶችን እንዲያገኙ ለማድረግ በማሰብ የከተማ ግብርና ስራ በየቦታው እየተስፋፋ ነው።

ይህ የምርት እድገትን የሚያመጣ ጥሩ ስራ ስለመሆኑ የሚያነሱት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የምግብና ሥነ-ምግብ ማዕከል ተባባሪ ፕሮፌሰሩ አሻግሬ ዘውዱ(ዶ/ር) የምርቱን ያህል ከእንስሳቱ ስለሚተላለፉብን በሽታዎች ግን ብዙም እየተጨነቅን አይደለም ይላሉ።

ከዶሮ የሚመጣ ጉንፋን አለ፣ አሁን በብዛት አካባቢዎቻችን ላይ ዶሮ የሚያረቡ ሰዎች ለጉንፋን ህመም ደጋግመው ሲጋለጡ እያየን ነው ይላሉ።

የጉንፋን ህመም እንደ በፊቱ በቀላሉ ይዞ የሚለቅ አይነት መሆኑ እየተለወጠ መምጣቱንም ያስረዳሉ።

ከብቶችም ወደ መኖሪያችን የበለጠ እየቀረቡ በመጡ ቁጥር የሚያስተላልፉት በሽታ ብዙ ነው የሚሉት ባለሞያው እንደ አዲስ አበባ ባለ ሰው ተቀራርቦ በሚኖርበት ቦታ ይህንን ማድረግ አደገኛ በው ብለዋል።

የሌማት ትሩፋት የሚያመጣው ጥሩ ውጤት ቢኖርም እንስሳቶቹ በተገቢው መንገድ መከተባቸውን የማረጋገጥ አቅማችን ደካማ በመሆኑ በጊዜ ሂደት የሚመጣው አደጋ ያስፈራኛል ብለዋል።

የከተማ ግብርና ከተሰራ መሰራት ያለበት በአትክልት እና መሰል ምርቶች እንጂ በእንስሳት መሆኑ አደጋ አለው ብለውናል።

Comments

Avatar