የውጪ ሃገር ዜጎች በኢትዮጵያ የማይንቀሳቀሰ ንብረት ባለቤት የሚሆኑበትን አግባብ ለመደንገግ የቀረበው ረቂቅ አዋጅ ለዝርዝር እይታ ተመራ
TRACK

የውጪ ሃገር ዜጎች በኢትዮጵያ የማይንቀሳቀሰ ንብረት ባለቤት የሚሆኑበትን አግባብ ለመደንገግ የቀረበው ረቂቅ አዋጅ ለዝርዝር እይታ ተመራ

Avatar

ግንቦት 12 2017

የውጪ ሃገር ዜጎች በኢትዮጵያ የማይንቀሳቀሰ ንብረት ባለቤት የሚሆኑበትን አግባብ ለመደንገግ የቀረበው ረቂቅ አዋጅ ለዝርዝር እይታ ተመራ፡፡

የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት በ4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 30ኛ መደበኛ ስብሰባው የውጪ ሃገር ዜጎች በኢትዮጵያ የማይንቀሳቀሰ ንብረት ባለቤት የሚሆኑበትን አግባብ ለመደንገግ የቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቷል፡፡

በዚህም ወቅት አንድ የምክር ቤት አባል ረቂቅ አዋጁ በዚህ ጊዜ ለውይይት መቅረቡ ተገቢ አይደለም የሚል ትችት ሰንዝረዋል፤ የውጭ ሃገር ካፒታል ወደ ሃገር ቤት ለማምጣት ታስቦ የተሰናዳ ቢሆንም የቤት ዋጋ በእጅጉ በናረበት በዚህ ጊዜ የማህበረሰቡን የቤት ባለቤትነት አቅም ሊፈታተን ይችላል ብለዋል፡፡

የምክር ቤት አባሉ በቅኝ ግዛት ውስጥ የነበሩ ሃገራትን ተሞክሮ በመጥቀስ ነዋሪውን ከመሃል ሃገር በማፈናቀል በውጭ ዜጎች መተካትን እንዳያመጣ ስጋት እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡

Comments

Avatar