ነሐሴ 6፣2016
በግብርና ኢንቨስትመንት ላይ የተሰማራው ‘ፍሬል ኢትዮጵያ’፤ በቂ የሰለጠነ የሰው ኃይል ባለማግኘቱ ከሌሎች ሀገራት ባለሞያዎችን ለማምጣት እየተገደደ መሆኑን ተናገረ፡፡
‘ፍሬል ኢትዮጵያ እርሻና ማቀነባበሪያ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር’፤ አሁን እንዲያለማው ከተሰጠው 10,000 ሄክታር መሬት በተጨማሪ በሚቀጥሉት ዓመታት ተጨማሪ 20,000 ሄክታር መሬት ከመንግስት ለመውሰድ አቅዷል፡፡
ይህንን እቅዱን ለመፈፀም ሀገሪቱ ውስጥ በቂ የሰለጠነ የሰው ኃይል አቅርቦት ችግር አለ ያሉት የፍሬል ኢትዮጵያ እርሻና ማቀነባበሪያ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ቢዝነስ ኦፕሬሽን ማናጀር፤ አቶ ፋሲካ ስዩም በተለይም የተማረ የሰው ኃይል አቅርቦት እጥረት አጋጥሞናል ብለዋል፡፡
ማህበሩ ዋንኛ የገበያ መዳረሻዎቹ አውሮፓ ቢሆንም፤ ይህንን መስፈርት አሟልቶ ምርት ለማምረት የሚያስችል ባለሞያ በበቂ ሁኔታ ከኢትዮጵያ ስላልተገኘ ከደቡብ አፍሪካ እና ከሌሎች ሀገራት ባለሙያ ለማምጣት እንደተገደዱ እንደሆነ አቶ ፋሲካ አስረድተዋል።
ፍሬል ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ ያሉ ቴክኖሎጂዎችን ለመተግበር እየሞከረ ነው ያሉት አቶ ፋሲካ ለአብነትም የድሮን ቴክኖሎጂን በመጠቀም የተለያዩ የኬሚካል እርጭቶችን እያደረገ ነው፡፡
Comments