ሴቶች በኪነ ጥበብ ስራዎች ላይ ያላቸውን ሚና እና ውክልናን በተመለከተ ለፖሊሲ አጥኒዎች ግብዓት ይሆናሉ የተባሉ ጥናቶች
TRACK

ሴቶች በኪነ ጥበብ ስራዎች ላይ ያላቸውን ሚና እና ውክልናን በተመለከተ ለፖሊሲ አጥኒዎች ግብዓት ይሆናሉ የተባሉ ጥናቶች

Avatar

መጋቢት 14፣2016

ሴቶች በኪነ ጥበብ እና በፈጠራ ስራዎች ላይ ያላቸውን ሚና እና ውክልናን በተመለከተ ለፖሊሲ አጥኒዎች ግብዓት ይሆናሉ የተባሉ ጥናቶች ሊደረጉ ነው ተባለ፡፡

ይደረጋሉ የተባሉ ጥናቶች ኢትዮጵያን ጨምሮ በ7 የአፍሪካ ሀገራት፤ ሴቶች በኪነ ጥበቡ ዘርፍ ያላቸውን ውክልና የሚዳስስ እንደሆነም ተነግሯል፡፡

ሴቶች፤ በሙዚቃ፣ በፊልም፣ በፋሽን ኢንዱስትሪ፣ በስዕል፣ በስነ ፁሑፍ እና በመሰል ኪነጥበባዊ ስራዎች ላይ ሴቶች ያላቸውን ዉክልና በጥናቶቹ እንደሚጠኑ ተጠቅሷል፡፡

የ3 ዓመት የጊዜ ገደብ ተቀምጦለታል በተባለው ይህ ጥናት በዘርፉ ሴቶች የሚገጥሟቸው ዕድሎች እንዲሁም ፈተናዎችንም እንደሚለይ ታልሞለታል ተብሏል፡፡

#Ethiopia #ShegerWerewoch #ሴቶችና_ኪነጥበብ #ሴቶች #ጥናት

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram:  https://tinyurl.com/yc6tfzsw

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

Comments

Avatar