ኢትዮዽያ በሎጅስቲክስ ሥራ ዛሬም ከዓለም 167 ሀገሮች 126ተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች ተባለ
TRACK

ኢትዮዽያ በሎጅስቲክስ ሥራ ዛሬም ከዓለም 167 ሀገሮች 126ተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች ተባለ

Avatar

ግንቦት 25 2017

ኢትዮዽያ በሎጅስቲክስ ሥራ ዛሬም ከዓለም 167 ሀገሮች 126ተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች ተባለ።

በሎጅስቲክስ ማእዘን አራት ደረጃዎችን አሻሽላ ነው 126 ነች የተባለው።

ይህ የተሰማው ዛሬ የኢትዮዽያ ብሔራዊ ሎጅስቲክስ ባለሞያዎች ማህበር ከባህርዳር ዩኒቨርሲቲና ከሚመለከታቸው ጋር በመከረበት ወቅት ነው።

የኢትዮዽያን ኢኮኖሚ ለማሳደግ በተለይ በሎጅስቲክስ ማእዘን ለውጥ እንዲመጣ እየተመከረ ነው ተብሏል።

የኢትዮዽያ የሎጅስቲክስ ኢንዱስትሪ ከፍ እንዲል አቅምና ተወዳዳሪነትን ለመፍጠር ፖሊሲዎችም እንዲሻሻሉ በማሰብ የጥናት ወረቀቶች ቀርበዋል።

በሎጅስቲክ ስራ ምርት ወይም አገልግሎትን በማደራጀት፤ በማሳደግ ከአገልግሎት አቅራቢዎች ወይም ከአምራቾች እስከ ደንበኛ ማጓጓዝ፤ ማስተላለፍ፣ ማሰራጨት ማቅረብ እና ማስተዳደር በኩል ኢትዮዽያ ዛሬም የምትፈተንበት እንደሆነ ተሰምቷል።

ተህቦ ንጉሴ

Comments

Avatar